Skip to main content

እንኳን ወደ  

ዘመን ሐበሻ በድህና መጡ  !

ዘመን ሓበሻ ስም ብቻ አይደለም። ማንነታችንን፣ ማኅበረሰባችንንና ግንኙነታችንን የሚያገናኝ የጋራ መድረክ ነው። ኤርትራውያንም ሆናችሁ ኢትዮጵያውያን፣ ወይም ደግሞ የዚህ ውብ ባህል ፍቅር ያላችሁ ሁሉ፤ ዓላማችን ፍቅርን፣ ትውፊትን እና የበለፀገውን የሓበሻ ባህል በዕለት ተዕለት ሕይወታችሁ ውስጥ እንዲንጸባረቅ ማድረግ ነው።

አገልግሎት

አዋቂ

የአዋቂዎች አገልግሎታችን ግለሰቦች በግልም ሆነ በሙያዊ ሕይወታቸው እንዲያድጉ የሚረዱ ተግባራዊ ኮርሶችን ያቀርባል። ከስሜታዊ ብልህነት  እስከ አመራር እና የሕይወት ክህሎቶች ያሉ ፕሮግራሞቻችን፤ ቀጣይነት ያለው ትምህርትን  እና ስኬትን ለመደገፍ ተቀርፀው የተዘጋጁ ናቸው።

ልጆች

የልጆች አገልግሎታችን ትምህርትን አስደሳች እና ትርጉም ያለው ለማድረግ የተነደፈ ነው። ልጆች እውቀትን፣ ፈጠራን፣ በራስ መተማመንን እና መሰረታዊ የሕይወት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ የሚረዱ የቋንቋ ትምህርቶችን፣ ትምህርታዊ እንቆቅልሾችን እና ሌሎች በይነተገናኝ  ፕሮግራሞችን እናቀርባለን።

የሀበሻ ገበያ

የሀበሻ ገበያችን ሓቀኛ የሀበሻ መግብቶችን፣ ትምህርታዊ እንቆቅልሾችን፣ ባህላዊ ምርቶችን እና መሰረታዊ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦች ያቀርባል። የታመኑ ምርቶችን ለማህበረሰባችን በቀላሉ ተደራሽ በማድረግ፣ ቅርሳችንን እና ማንነታችንን ለመጠበቅ እንረዳለን።

ራዕይ

በስሜታዊ ብልህነት ፣ በንጹር አተሓሳስባ፣ በዕድሜ ልክ ትምህርት እና በጋራ ብልጽግና አማካኝነት፤ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች የኵናት፣ የድኽነት፣ የመከፋፈል እና የመፈናቀል ዘላቂ ሳዕቤኖችን (ተፅዕኖዎችን) የሚያሸንፉበት፤ የዳነ (የፈወሰ)፣ የተባበረ እና የበለጸገ የሀበሻ ማህበረሰብ ለመገንባት


    ሰው የማደግ፣ የበኩሉን አስተዋጽኦ የማበርከት እና የተሻለ ወደፊትን የመገንባት ዕድል የሚያገኝበት፤ የዳነ (የተፈወሰ)፣ የተባበረ እና የበለጸገ የሀበሻ ማህበረሰብ።

ተልዕኮ

ዘመን ሀበሻ በስሜታዊ ብልህነት ፣ በንጹር አተሓሳስባ፣ በትምህርት፣ በተግባራዊ ምርቶች፣ በዲጂታል አገልግሎቶች እና በማህበረሰብ ትብብር አማካኝነት የሀበሻን ማህበረሰብ ያጠናክራል እንዲሁም ያበቃል ። ከስደት (ዲያስፖራ) በመነሳት፤ ሰዎች እንዲያገግሙ (እንዲፈወሱ)፣ በንጹር እንዲያስቡ፣ አብረው እንዲያድጉ፣ እንዲሁም ጠንካራ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቦችን እንዲገነቡ እንረዳለን። በተጨማሪም ቅርሳችንን ለመጠበቅ በሚያግዝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የማህበረሰባችንን ፍላጎቶች በሚያሟላ መልኩ፤ እውነተኛ የሀበሻ ምግቦችን፣ ባህላዊ ምርቶችን እና መሰረታዊ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን እናቀርባለን። በጋራ በመሆን ጤናማ፣ ጠንካራ እና የተሳሰረ መጻኢ (ወደፊት) እየገነባን እንገኛለን።

አጋሮቻችን

ተጫወት እና ተማር

ተጨማሪ ይመልከቱ

ስሜታዊ ብልህነት

ተጨማሪ ይመልከቱ

መጪው ግዝያቹ በእጃቹ ነው፤ ከኛ ጋር ሆነው ይገንቡት።

ዘመን ሓበሻ በቀላል ሃሳብ ነው የተጀመረው፦ የሓበሻን ባህል በዕውቀትና በማኅበረሰቡ አቅፎ የያዘ፣ የበለፀገ ማንነቱን የሚያሳይ ቦታ መፍጠር። ከአንድ ትንሽ ፍላጎት ተነስተን፣ ዛሬ አንድ ትልቅ ዓላማ ይዘን ወደ ተለያዩ ቦታዎችና አገልግሎቶች ተስፋፍተን እንገኛለን። እሱም ለአካባቢያችን መታወቂያ፣ ለነጋዴዎቻችን ደግሞ በማገዝ ትውፊታችንን ለዓለም ማስተዋወቅ ነው።