አገልግሎት
ራዕይ
በስሜታዊ ብልህነት ፣ በንጹር አተሓሳስባ፣ በዕድሜ ልክ ትምህርት እና በጋራ ብልጽግና አማካኝነት፤ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች የኵናት፣ የድኽነት፣ የመከፋፈል እና የመፈናቀል ዘላቂ ሳዕቤኖችን (ተፅዕኖዎችን) የሚያሸንፉበት፤ የዳነ (የተፈወሰ)፣ የተባበረ እና የበለጸገ የሀበሻ ማህበረሰብ ለመገንባት
- ሰው የማደግ፣ የበኩሉን አስተዋጽኦ የማበርከት እና የተሻለ ወደፊትን የመገንባት ዕድል የሚያገኝበት፤ የዳነ (የተፈወሰ)፣ የተባበረ እና የበለጸገ የሀበሻ ማህበረሰብ።
ተልዕኮ
ዘመን ሀበሻ በስሜታዊ ብልህነት ፣ በንጹር አተሓሳስባ፣ በትምህርት፣ በተግባራዊ ምርቶች፣ በዲጂታል አገልግሎቶች እና በማህበረሰብ ትብብር አማካኝነት የሀበሻን ማህበረሰብ ያጠናክራል እንዲሁም ያበቃል ። ከስደት (ዲያስፖራ) በመነሳት፤ ሰዎች እንዲያገግሙ (እንዲፈወሱ)፣ በንጹር እንዲያስቡ፣ አብረው እንዲያድጉ፣ እንዲሁም ጠንካራ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቦችን እንዲገነቡ እንረዳለን። በተጨማሪም ቅርሳችንን ለመጠበቅ በሚያግዝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የማህበረሰባችንን ፍላጎቶች በሚያሟላ መልኩ፤ እውነተኛ የሀበሻ ምግቦችን፣ ባህላዊ ምርቶችን እና መሰረታዊ የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን እናቀርባለን። በጋራ በመሆን ጤናማ፣ ጠንካራ እና የተሳሰረ መጻኢ (ወደፊት) እየገነባን እንገኛለን።

አጋሮቻችን

ተጫወት እና ተማር

ስሜታዊ ብልህነት

መጪው ግዝያቹ በእጃቹ ነው፤ ከኛ ጋር ሆነው ይገንቡት።
ዘመን ሓበሻ በቀላል ሃሳብ ነው የተጀመረው፦ የሓበሻን ባህል በዕውቀትና በማኅበረሰቡ አቅፎ የያዘ፣ የበለፀገ ማንነቱን የሚያሳይ ቦታ መፍጠር። ከአንድ ትንሽ ፍላጎት ተነስተን፣ ዛሬ አንድ ትልቅ ዓላማ ይዘን ወደ ተለያዩ ቦታዎችና አገልግሎቶች ተስፋፍተን እንገኛለን። እሱም ለአካባቢያችን መታወቂያ፣ ለነጋዴዎቻችን ደግሞ በማገዝ ትውፊታችንን ለዓለም ማስተዋወቅ ነው።


